1 ዜና መዋዕል 4:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቆጽም ዓኑብና ጾቤባ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እንዲሁም ቆጽ የሃሩም ልጅ የአሐርሔል ዘሮች ለሆኑት ጐሣዎች የነገድ አባት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቆጽ ወንዶች ልጆች ዓኑብ፣ ጾቤባና፣ የሃሩም ልጅ የአሐርሔል ጐሣዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቆጽ ዓኑብን፥ ጾቤባን፥ የሃሩምንም ልጅ የአሐርሔልን ወገኖች ወለደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቆስ፥ ኢኖብን፥ ሲባባን፥ የሃሩምንም ልጅ የሬካብን ወንድም ወገኖች ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቆጽ ዓኑብን፥ ጾቤባን፥ የሃሩምንም ልጅ የአሐርሔልን ወገኖች ወለደ። |
ከቤተሰቡ መካከል እጅግ የተከበረ ያዕቤጽ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እናቱ እርሱን በወለደች ጊዜ ከባድ የምጥ ጣር ደርሶባት ስለ ነበር “ያዕቤጽ” የሚል ስም አወጣችለት፤
ከዚህ የሚከተሉት የካህናት ጐሣዎች ሐባያ፥ ሀቆጽና ባርዚላይ የቀድሞ አባቶች እነማን እንደ ነበሩ ካለማወቃቸውም የተነሣ ካህናት ሆነው ለማገልገል ተቀባይነት አላገኙም። (ባርዚላይ ከገለዓዳዊው የባርዚላይ ልጆች አንድዋን አግብቶ በዚሁ ስም ይጠራ ነበር)።