1 ዜና መዋዕል 4:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሾባል ረአያን ወለደ፤ ረአያም ያሐትን ወለደ፤ ያሐትም በጾርዓ ለሚኖሩት ሕዝቦች የቀድሞ አባቶች የነበሩትን አሑማይንና ላሃድን ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሦባል ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤት ደግሞ አሑማይንና ላሃድን ወለደ፤ እነዚህም የጾርዓውያን ጐሣዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሦባልም ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትም አሑማይንና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የጾርዓውያን ወገኖች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሱባልም ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትም አሑማይንና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የሰራአውያን ትውልዶች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሦባልም ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትም አሑማይንና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የጾርዓውያን ወገኖች ናቸው። |
ሑር የካሌብና የኤፍራታ በኲር ልጅ ነው፤ ከእርሱ ልጆች መካከል በቤተልሔም የሰፈሩ አሉ፤ ሌሎቹም የሑር ልጆች ጰኑኤልና ዔዜር ናቸው፤ የኤታም ወንዶች ልጆች ኤይዝርኤል፥ ኢሻማ፥ ኤድባሽ፥ ጌዶርን የመሠረተው ፋኑኤልና ሑሻን የመሠረተው ኤጼር ሲሆኑ ሐጽሌልጶኒ የምትባል እኅት ነበረቻቸው።