1 ዜና መዋዕል 2:52 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቂርያትይዓሪም አባት ሾባል ሌሎችም ልጆች ነበሩት፦ እነርሱም ሔሮኤትና የመኑሖት ጐሣዎች እኩሌታ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቂርያትይዓይሪም አባት የሦባል ዘሮች፤ የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኩሌታ፣ ሀሮኤ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቂርያት-ይዓሪምም አባት ለሦባል ልጆች ነበሩት፤ ሀሮኤ የመናሕታውያን እኩሌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀርያታርምም አባት የሶባል ልጆች አረኤ፥ ሃጼ፥ አማኒት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቂርያትይዓሪምም አባት ለሦባል ልጆች ነበሩት፤ ሀሮኤ የመናሕታውያን እኵሌታ። |
እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ቤተሰቦች ዩትራውያን፥ ፑታውያን፥ ሹማታውያንና ሚሽራዓውያን ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤ ከእነርሱም የጾርዓና የኤሽታኦል ትውልድ ተገኙ።
ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጒዞ ጀምረው ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሕዝብ ወደሚኖሩባቸው ከተሞች ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ በኤሮትና ቂርያትይዓሪም ተብለው ይጠሩ ነበር፤