ዘካርያስ 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስቀሎና አይታ ትፈራለች፤ ጋዛ በሥጋት ትታመማለች፤ እንዲሁም አቃሮን፥ ተስፋዋ ይመነምናል። ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚኖር አይገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስቀሎና አይታ ትርዳለች፤ ጋዛ በሥቃይ ትቃትታለች፤ አቃሮናም እንደዚሁ ትሠቃያለች፤ ተስፋዋ ይመነምናልና። ጋዛ ንጉሥዋን ታጣለች፤ አቃሮንም ባድማ ትሆናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአስቀሎና ከተማ ይህን አይታ ትፈራለች፤ የጋዛ ከተማም ይህን በማየት እጅግ ትጨነቃለች፤ ዔቅሮንም እንዲሁ ተስፋ ትቈርጣለች፤ ጋዛ ንጉሥዋን ታጣለች፤ አስቀሎናም ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አስቀሎና አይታ ትፈራለች፣ ጋዛ ደግሞ አይታ እጅግ ትታመማለች፣ አቃሮንም እንዲሁ፥ ተስፋዋ ይቈረጣልና፣ ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚቀመጥ አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስቀሎና አይታ ትፈራለች፥ ጋዛ ደግሞ አይታ እጅግ ትታመማለች፥ አቃሮንም እንዲሁ፥ ተስፋዋ ይቈረጣልና፥ ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚቀመጥ አይገኝም። |
ጢሮስና ሲዶና የፍልስጥኤምም ግዛት ሁሉ ሆይ፥ ከእናንተ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ? በውኑ ልትበቀሉኝ ትፈልጋላችሁን? በቀልን በእኔ ላይ ማውረድ ብትሞክሩ፥ በቀሉን መልሼ በፍጥነት በእናንተ ላይ አወርደዋለሁ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ለኤዶምያስ አሳልፈው ለመስጠት መላውን ሕዝብ ማርከው ወስደዋልና ስለ ሦስት የጋዛ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።
ነዋሪዎችዋን ከአዛጦን፥ በትረ መንግሥት የያዘውንም ከአስቀሎና አጠፋለሁ፤ እጄንም በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፥ ከፍልስጥኤማውያንም የቀሩት ይጠፋሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በምንም ዓይነት ነገር አላፍርም፤ ነገር ግን በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ እንደ ወትሮው እንዲሁ አሁንም በሥጋዬ ይከብራል ብዬ በሙሉ ድፍረት እናገራለሁ።