እኔስ እንዴት እሆናለሁ? ነውሬንስ ተሸክሜ የት እገባለሁ? አንተም ብትሆን በእስራኤል ከወራዳዎቹ እንደ አንዱ ትቆጠራለህ፤ እባክህ ለንጉሡ ጠይቀው፤ እኔንም አይከለክልህም።”
ዘካርያስ 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንቺ ደግሞ በቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስረኞችሽን ውኃ ከሌለበት ጉድጓድ አውጥቻለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአንቺ ደግሞ፣ ከአንቺ ጋራ ከገባሁት የደም ቃል ኪዳን የተነሣ፣ እስረኞችሽን ውሃ ከሌለበት ጕድጓድ ነጻ እለቅቃቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በመሥዋዕት ደም ከአንቺ ጋር ቃል ኪዳን ስለ ገባሁ፥ ውሃ ከማይገኝበት ጒድጓድ እስረኞችሽን ነጻ አወጣለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአንቺም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስሮችሽን ውኃ ከሌለበት ጕድጓድ አውጥቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአንቺም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስሮችሽን ውኃ ከሌለበት ጕድጓድ አውጥቻለሁ። |
እኔስ እንዴት እሆናለሁ? ነውሬንስ ተሸክሜ የት እገባለሁ? አንተም ብትሆን በእስራኤል ከወራዳዎቹ እንደ አንዱ ትቆጠራለህ፤ እባክህ ለንጉሡ ጠይቀው፤ እኔንም አይከለክልህም።”
ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፤ ሁሉም በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል፤ በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፤ ተበዝብዘዋል የሚያድንም የለም፥ ተማርከዋል፤ “መልሷቸው” የሚል ማንም የለም።
የተሰሩትንም፦ ‘ውጡ’ በጨለማም የተቀመጡትን፦ ‘ተገለጡ’ እንድትል ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ። በመንገድም ላይ ይሰማራሉ፥ ማሰማርያቸውም በገላጣ ኮረብታ ሁሉ ላይ ይሆናል።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ጌታ ቀብቶኛልና፥ ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።
ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በእስር ቤቱም አደባባይ ወደነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጉድጓድ ውስጥ ኤርምያስን በገመድ አውርደው ጣሉት። በጉድጓድም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።
እርሱም እየጮኸ ‘አብርሃም አባት ሆይ! ማረኝ፤ በዚህ ነበልባል እሠቃያለሁና የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ላክልኝ፤’ አለ።
“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች መልካም ዜናን እንዳበሥር ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዐይነ ስውሮችም ማየትን እንዳውጅ፥ የተጨቆኑትንም ነጻ እንዳወጣ
እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሰረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ።
አንተ ግን እዚህ እኔ አጠገብ ቁም፤ እኔ በምሰጣቸው ምድር እነዚህን በመጠበቅ እንዲኖሩ፥ ሕግጋቴን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቶቼን ሁሉ እነግርሃለሁ።’
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፥ የተቀደሰበትን ያንን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቆጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያስቆጣ፥ ቅጣቱ እጅግ የከፋ እንዴት የማይሆን ይመስላችኋል?
ሺህ ዓመትም አሰረው፤ ወደ ጥልቅም ጣለው፤ አሕዛብንም ወደ ፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማኅተም አደረገበት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ መፈታት ይገባዋል።