ደግሞም ለአባቶቻቸው አምላክ ለጌታ ለመሠዋት ከእስራኤል ነገድ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ልባቸውን የሰጡ ሁሉ እነርሱን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ዘካርያስ 8:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሰዎችም፦ “ጌታን ለመለመን፥ የሠራዊት ጌታንም ለመፈለግ ኑ እንሂድ፤ እኔም እሄዳለሁ” እያሉ ወደ ሌላ ከተማ ይሄዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአንዲቱ ከተማ ነዋሪዎችም፣ ‘እግዚአብሔርን ለመለመን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ለመፈለግ፣ ኑ፤ በፍጥነት እንሂድ፤ እኔም ራሴ እሄዳለሁ’ እያሉ ወደ ሌላዪቱ ከተማ ይሄዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንድ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ሌላ ከተማ ሄደው ‘ኑ! ከሠራዊት አምላክ ቸርነትን እንለምን፤ እኛም ወደዚያ መሄዳችን ነው!’ ይሉአቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንዲትም ከተማ የሚኖሩ ሰዎች፦ እግዚአብሔርን እንለምን ዘንድ፥ የሠራዊትንም ጌታ እግዚአብሔርን እንፈልግ ዘንድ ኑ እንሂድ፣ እኔም እሄዳለሁ እያሉ ወደ ሌላ ከተማ ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንዲትም ከተማ የሚኖሩ ሰዎች፦ እግዚአብሔርን እንለምን ዘንድ፥ የሠራዊትንም ጌታ እግዚአብሔርን እንፈልግ ዘንድ ኑ እንሂድ፥ እኔም እሄዳለሁ እያሉ ወደ ሌላ ከተማ ይሄዳሉ። |
ደግሞም ለአባቶቻቸው አምላክ ለጌታ ለመሠዋት ከእስራኤል ነገድ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ልባቸውን የሰጡ ሁሉ እነርሱን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
እኛም እንወቅ፤ ጌታን ለማወቅ እንትጋ፤ እንደ ንጋትም መገለጡ እርግጥ ነው፤ እንደ ዝናብ ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ በልግ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”