ዘካርያስ 5:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የእርሳሱን መክሊት አነሡት፥ እነሆም፥ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከእርሳስ የተሠራው ክዳን ተነሣ፤ የኢፍ መስፈሪያ ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቅርጫቱ ከእርሳስ የተሠራ መክደኛ ነበረው፤ እኔም እያየሁት መክደኛው ተከፈተ፤ እነሆም በቅርጫቱ ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፥ የእርሳሱን መክሊት አነሡት፣ እነሆም፥ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ የእርሳሱን መክሊት አነሡት፥ እነሆም፥ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር። |
በአሮጌው ኩሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መከማቻ ሠራችሁ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፥ ቀድሞ አቅዶ የሠራውንም አላስታወሳችሁም።
እኔም፦ “ምንድን ናት?” አልኩት። እርሱም፦ “ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት” አለኝ። ደግሞም፦ “ይህ ነው በምድር ሁሉ ያለ የእነርሱ በደል” አለ።