ዘካርያስ 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልአኩም መልሶ በፊቱ የቆሙትን፦ “እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ” አላቸው። እርሱንም፦ “እነሆ፥ አበሳህን ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልአኩም ከፊቱ ቆመው የነበሩትን፣ “ያደፉ ልብሶቹን አውልቁለት” አላቸው። ኢያሱንም፣ “እነሆ፤ ኀጢአትህን ከአንተ አስወግጃለሁ፤ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም በፊቱ ቆመው የሚያገለግሉትን “ይህን ያደፈ ልብስ አውልቁለት!” ብሎ አዘዛቸው፤ ወደ ኢያሱም መለስ ብሎ “እነሆ በደልህን አስወግጄልሃለሁ፤ አዲስ የክብር ልብስም አለብስሃለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን፦ እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው። እርሱንም፦ እነሆ፥ አበሳህን ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ አለው። |
ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ጌታ የሚለውን ስማ! ጌታ በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፥ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፤
ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።
አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።
ጌታ ለክብሩ የተከላቸው ጽድቃዊ የባሉጥ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች በአመድ ፋንታ አክሊልን እንዳደርግላቸው፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘን መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እንድሰጣቸው ልኮኛል።
ካህናቱም ከገቡ በኋላ የሚያገለግሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ከመቅደሱ ወደ ውጭው አደባባይ አይወጡም፥ የተቀደሱ ናቸውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ሲቀርቡ ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱን ትሩፍ ዓመጽ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ርኅራኄ ይወድዳልና ቁጣውን ለዘለዓለም አያቆይም።
“የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፤ እኔም በዚህ ስፍራ ከቆሙት ጋር ስፍራን እሰጥሃለሁ።”
በኢያሱ ፊት ያኖርሁትን ድንጋይ ተመልከት፤ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዐይኖች አሉ፤ እነሆ፥ ቅርጹን እቀርጻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።
ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋል።
አየሁም፤ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቁጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፤
እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። እንዲህም አለኝም፦ “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሶቻቸውንም አጥበው በበጉ ደም አንጽተዋል።