ዘካርያስ 14:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ስለሚደርስ፥ በተራሮች መካከል ባለው ሸለቆ ትሸሻላችሁ። በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን በምድር መንቀጥቀጥ ምክንያት ከሆነው ሽሽት በበለጠ ትሸሻላችሁ። ከዚያም አምላኬ ጌታ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም በእግዚአብሔር ተራራ ሸለቆ በኩል በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን በምድር ትሸሻላችሁ፤ ሸለቆው እስከ አጸል ይደርሳልና። በምድር መናወጥ ምክንያት ሸሽታችሁ እንደ ነበረ ትሸሻላችሁ፤ ከዚያም አምላኬ እግዚአብሔር ይመጣል፤ ቅዱሳኑም ሁሉ ዐብረውት ይመጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም ተራራውን በሁለት ከፍሎ እስከ አጻል በደረሰው በዚህ ሸለቆ ውስጥ አልፋችሁ ታመልጣላችሁ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያ ዘመን ምድር በተናወጠች ጊዜ የቀድሞ አባቶቻችሁ በሸሹት ዐይነት ትሸሻላችሁ፤ እግዚአብሔር አምላኬም ቅዱሳኑን አስከትሎ ይመጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳልና በተራሮች ሸለቆ ትሸሻላችሁ፣ በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከሆነው ከምድር መናወጥ ፊት እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ፣ አምላኬ እግዚአብሔርም ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳልና በተራሮች ሸለቆ ትሸሻላችሁ፥ በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከሆነው ከምድር መናወጥ ፊት እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ፥ አምላኬ እግዚአብሔርም ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል። |
ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።
የአሞጽ ቃላት፥ በቴቁሔ ከሚገኙ ከበግ አርቢዎች መካከል የነበረ፥ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ የምድር መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል ያየው ይህ ነው።
በሻፊር የምትቀመጪ ሆይ፥ በራቁትነትና በእፍረት እለፊ፤ በጻኣናን የምትቀመጠው አልወጣችም፤ የቤትሐኤጼል ለቅሶ የመቆሚያ ስፍራውን ከእናንተ ይወስዳል።
ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎችም፦ ‘ሞገስ ይሁንለት! ሞገስ ይሁንለት!’ ብለው እየጮኹ እርሱ የመደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል” ብሎ ነገረኝ።
በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው “እስቲ ንገረን፤ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድነው?” አሉት።
እንዲህም አለ፦ “ጌታ ከሲና ተራራ መጣ፥ በሴይርም እንደ ንጋት ተገለጠ፥ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ በስተቀኙም ከእሳት ነበልባል ጋር፥ ከአእላፋት ቅዱሳኑም ጋር መጣ።
በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።
ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት የመፍረድ ሥልጣን ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርነትና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ እንዲሁም ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ እንደገና ሕያው ሆነው ከክርስቶስም ጋር ለሺህ ዓመት ነገሡ።