ዘካርያስ 14:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምድርም ወገኖች ሁሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም ለማይወጡ ለእነርሱ ዝናብ አይዘንብላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድር ሕዝብ ሁሉ ለንጉሡ፣ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ሊሰግዱ ወደ ኢየሩሳሌም የማይወጡ ከሆነ ዝናብ አያገኙም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለንጉሡ ለሠራዊት አምላክ የማይሰግዱለት ሕዝቦች ቢኖሩ በምድራቸው ዝናብ አይዘንብላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምድርም ወገኖች ሁሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ለማይወጡ ለእነርሱ ዝናብ አይዘንብላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምድርም ወገኖች ሁሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ለማይወጡ ለእነርሱ ዝናብ አይዘንብላቸውም። |
ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፥ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።
በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው ጌታ ስም እነግርሃለሁ” አለው።
“አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት ዝናብ እንዳይዘንብላቸው አድርገህ በምትቀጣቸው ጊዜ፥ በፈጸሙት በደል በመጸጸት ፊታቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰው በትሕትና ቢለምኑህ፥
“በአንተ ላይ ኃጢአት ስለ ሠሩ ሰማያት በተዘጉ ጊዜ ዝናብም ባልዘነበ ጊዜ፥ ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩ፥ ስምህንም ቢጠሩ፥ ባሠቃየሃቸውም ጊዜ ከኃጢአታቸው ቢመለሱ፥
በዚያን ጊዜ ለሠራዊት ጌታ፥ ከረጅምና ከለስላሳ ሕዝብ፥ ከቅርብም ከሩቅም አስፈሪ ከሆነ ሕዝብ፥ ኀያል ከሆነና ከሚገዛ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ከሚከፍሉት ሕዝብ ዘንድ ስጦታ ይመጣለታል፤ ስጦታውም የሠራዊት ጌታ ስም ወደሚገኝበት ወደ ጽዮን ተራራ ይቀርባል።
ያዕቆብን በልተውታልና፥ ውጠውታልምና፥ አጥፍተውታልምና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አውርድ።
በውኑ በአሕዛብ ከንቱ ጣዖታት መካከል ዝናብን ሊያዘንብ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ካፊያን መስጠት ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ! አንተ አይደለህምን? አንተ እነዚህን ሁሉ ነገሮች አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።
ታላላቆቻቸውም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ ላኩ፤ ወደ ጉድጓድ መጡ ውኃም አላገኙም፥ ዕቃቸውንም ባዶውን ይዘው ተመለሱ፤ አፈሩም ተዋረዱም ራሳቸውንም ተከናነቡ።
የጌታም ቁጣ በላያችሁ እንዳይነድ፤ እርሱም ዝናብ እንዳይከለክላችሁ፤ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም ጌታ ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ።”
እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የመዝጋት ሥልጣን አላቸው፤ ውሃዎችንም ወደ ደም ለመለወጥ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ምድርን የመምታት ሥልጣን አላቸው።