ዘካርያስ 11:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በአገር ውስጥ እረኛ አስነሣለሁ፤ እርሱም የጠፋውን አያስተውልም፥ የባዘነውን አይፈልግም፥ የተሰበረውን አይጠግንም፥ የዳነውንም አይቀልብም፤ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፥ ሰኰናውንም ይቀለጣጥማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ በምድሪቱ ላይ እረኛ አስነሣለሁ፤ እርሱም የጠፋውን አያስብም፤ የባዘነውን አይፈልግም፤ የተሰበረውን አይጠግንም፤ የዳነውንም አይቀልብም፤ ነገር ግን የሠባውን ሥጋ ይበላል፤ ሰኰናውንም ሳይቀር ይቀለጣጥማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ በምድሪቱ መንጋዬን የሚጠብቅ አንድ እረኛ አስነሣለሁ፤ ይህን በማድረግ ፈንታ እርሱ ስለ ጠፉት አያስብም፤ የባዘኑትን አይፈልግም፤ ያነከሱትን አይፈውስም፤ ጤናማዎችንም አይመግብም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ የወፈረውን እያረደ ይበላል፤ ሰኮናቸውንም ይቈራርጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ በአገሩ ውስጥ እረኛ አስነሣለሁ፣ እርሱም የጠፋውን አያስብም፥ የባዘነውን አይፈልግም፥ የተሰበረውን አይጠግንም፣ የዳነውንም አይቀልብም፥ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፥ ሰኰናውንም ይቀለጣጥማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በአገሩ ውስጥ እረኛ አስነሣለሁ፥ እርሱም የጠፋውን አያስብም፥ የባዘነውን አይፈልግም፥ የተሰበረውን አይጠግንም፥ የዳነውንም አይቀልብም፥ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፥ ሰኰናውንም ይቀለጣጥማል። |
እርሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፥ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ መጠንቀቅ ይኖርብኛል፤ ሰዎችም አንድ ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደሆነ እንሰሶቹ ሁሉ ይሞታሉ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸዋልም አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ ስለ ክፉ ሥራችሁ እጐበኛችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በእረኞች ላይ ነኝ፥ መንጋዎቼን ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ መንጋዎቼን ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ። ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያስማሩም፤ በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም።
የጠፋውን እፈልጋለሁ፥ የባዘነውን እመልሳለሁ፥ የተሰበረውንም እጠግናለሁ የደከመውንም አበረታለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውን አጠፋለሁ፤ በፍትሕም እጠብቀዋለሁ።