በጻድቁ በር ላይ እንደነበሩት ኃጢአተኞች፥ እነርሱም ታወሩ፤ ጨለማ ሊውጣቸው በዙሪያቸው ባሰፈሰፈ ጊዜም፥ በበሩ ለመውጣት እያንዳንዱ መንገድን በዳሰሳ ማግኘት ነበረበት።
ብርሃናት ከባሕርያቸው ተለውጠውባቸው ነበርና፤ የዜማውን ነገር በማወቅ የበገናው ስም እንደሚለወጥ፥ የቀናም ሆኖ በዜማው ጸንቶ እንደሚኖር በየወገናቸው የተፈጠሩትን በማየት ፈጽሞ የሚሰፈር ሥራም፥ እንዲሁ ነው።