ብቸኛው ብርሃናቸው፥ ድንገተኛው፥ አስፈሪውና ታላቁ ያ ትርዒት በጠፋ ጊዜም ከፍርሃታቸው የነሣ ምንም ጊዜ ካዩት ሁሉ እጅጉን አስደንጋጭ ሆነባቸው።
ነገር ግን ከዚህ ከሚታየው መልክ ይልቅ ግርማው ፍጹም የሆነ፥ ከማይታዩትም መልኮች ይልቅ የከፋ ብቸኛ እሳት ድንገት ታያቸው።