ፍጡርህ ያንተ የፈጣሪው አገልጋይ ነውና፥ ኃጥአተኛውን ለመቅጣት ይወጠራል፤ አንተን ለሚያምኑት ሲል ደግሞ ይላላል።
ፈጣሪ ሆይ፥ ፍጥረቱ ሁሉ ለአንተ ያገለግላልና፥ በዐመፀኞች ላይ የሚላክ ፍርድን ታመጣለህ፥ በአንተ ወደሚታመኑም ይደርስ ዘንድ ደስታን ትሰጣለህ።