እንጨት ጠራቢውን ተመልከቱ፥ ለሥራው የሚስማማውን ዛፍ ይጥላል፤ ቅርፊቱን ሁሉ በጥንቃቄ ይልጣል፤ በጥበብ ጠርቦና አስተካክሎም የቤት ውስጥ መገልገያ ያደርገዋል።
የሚታየውንና የሚወዛወዘውን እንጨት የሚጠርብ ጠራቢ ቢኖር መልካም ሆኖ የበቀለውን እንጨት ይቈርጣል፥ ቅርፊቱን ሁሉ በጥበብ ይጠርባል፤ መልካም አድርጎም ይሠራዋል፥ ለኑሮ አገልግሎትም የሚጠቅም ዕቃ አድርጎ ይሠራዋል።