ማሕልየ መሓልይ 8:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእኔ ያለኝ የወይን ቦታ በፊቴ ነው፥ ሰሎሞን ሆይ፥ ሺሁ ለአንተ፥ ሁለት መቶውም ፍሬውን ለሚጠብቁ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይኔ ተክል ቦታ የራሴ፣ የግሌ ነው፤ ሰሎሞን ሆይ፤ አንድ ሺሑ ሰቅል ለአንተ፤ ፍሬውን ለሚጠብቁ ደግም ሁለት መቶ ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የግሌ የሆነ የወይን ተክል ቦታ አለኝ፤ ሰሎሞን ሆይ! አንተ አንድ ሺህ ብር፥ አትክልተኞቹ ሁለት መቶ ብር ልትወስዱ ትችላላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእኔ ያለኝ የወይን ቦታ በፊቴ ነው፤ አንዱ ሺህ ለሰሎሞን፥ ሁለቱ መቶ ፍሬውን ለሚጠብቁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእኔ ያለኝ የወይን ቦታ በፊቴ ነው፥ ሰሎሞን ሆይ፥ ሺሁ ለአንተ፥ ሁለት መቶውም ፍሬውን ለሚጠብቁ ይሆናል። |
ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንኩ አትዩኝ፥ የእናቴ ልጆች ተጣሉኝ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፥ ነገር ግን የእኔን ወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።