ሣራንም አላት፦ እነሆ፥ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት፥ ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዐይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ፥ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና።”
ማሕልየ መሓልይ 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው፥ የወይኑን ቦታ ለጠባቂዎች አከራየው፥ ሰው ሁሉ ለፍሬው ሺህ ብር ያመጣለት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ተክል ቦታ ነበረው፤ የወይኑን ተክል ቦታም ለአትክልተኞች አከራየው፤ እያንዳንዳቸውም የፍሬውን ዋጋ፣ አንድ አንድ ሺሕ ሰቅል ብር ያመጡለት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን በባዓልሃሞን የወይን ተክል ቦታ ነበረው፤ የወይኑንም ተክል ቦታ ለአትክልተኞች አከራየው፤ እያንዳንዳቸውም አንድ ሺህ ብር ያመጡለት ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው፤ የወይኑን ቦታ ፍሬውን ለሚጠብቁ አከራየው፤ ሰው ሁሉ በየጊዜው ለፍሬው አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው፥ የወይኑን ቦታ ለጠባቂዎች አከራየው፥ ሰው ሁሉ ለፍሬው ሺህ ብር ያመጣለት ነበር። |
ሣራንም አላት፦ እነሆ፥ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት፥ ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዐይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ፥ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና።”
ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንኩ አትዩኝ፥ የእናቴ ልጆች ተጣሉኝ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፥ ነገር ግን የእኔን ወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
ከዚያም እንዲህ እያለ በምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፤ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ ዙሪያውን ዐጠረ፤ ለመጭመቂያው ጉድጓድ ቆፈረ፤ የመጠበቂያም ማማ ሠራለት፤ ከዚያም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።