ማሕልየ መሓልይ 8:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ቅጥር ነኝ ጡቶቼም እንደ ግንብ ናቸው፥ በዚያን ጊዜ በፊቱ ሰላምን እንደምታገኝ ሆንሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ እኔ ቅጥር ነኝ፤ ጡቶቼም እንደ ማማ ግንቦች ናቸው፤ እኔም በዐይኖቹ ፊት፣ ሰላምን እንደሚያመጣ ሰው ሆንሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ እኔ ቅጽር ነኝ፤ ጡቶቼም እንደ ቅጽር ማማዎች ናቸው፤ ከውዴ ጋር ስሆን እርሱ ደስታንና ሰላምን ያገኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ቅጥር ነኝ፥ ጡቶችም እንደ ግንብ ናቸው፤ በዚያ ጊዜ በፊቱ ሰላምን እንደምታገኝ ሆንሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ቅጥር ነኝ ጡቶቼም እንደ ግንብ ናቸው፥ በዚያን ጊዜ በፊቱ ሰላምን እንደምታገኝ ሆንሁ። |
በሜዳ ላይ እንዳለ ቡቃያ አበዛሁሽ፥ አንቺም አደግሽ ታላቅም ሆንሽ፥ በጌጦች አጌጥሽ፥ ጡቶችሽ አጐጠጐጡ፥ ጠጉርሽም አደገ፥ ሆኖም ዕርቃንሽንና ራቁትሽን ነበርሽ።
ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ ዋነኛ በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ በማሳየት፥ በእርሱ አምነው የዘለዓለም ሕይወትን ለሚያገኙ ምሳሌ እንድሆን አደረገኝ፥ በእዚህም ምክንያት ምሕረትን አገኘሁ።