Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 16:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በሜዳ ላይ እንዳለ ቡቃያ አበዛሁሽ፥ አንቺም አደግሽ ታላቅም ሆንሽ፥ በጌጦች አጌጥሽ፥ ጡቶችሽ አጐጠጐጡ፥ ጠጉርሽም አደገ፥ ሆኖም ዕርቃንሽንና ራቁትሽን ነበርሽ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሜዳ ላይ እንዳለ ቡቃያ አሳደግሁሽ፤ አንቺም አደግሽ፤ ብርቅ ዕንቍ ሆንሽ። ጡቶችሽ አጐጠጐጡ፤ ጠጕርሽም አደገ፤ ነገር ግን ከእናትሽ ማሕፀን እንደ ወጣሽ ዕርቃንሽን ነበርሽ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ምቾት እንዳለው ተክል እንድታድጊ አደረግሁ፤ ቁመትና ጠንካራ ሰውነት በመጨመር አድገሽ የተዋብሽ ወጣት ሆንሽ፤ ጡትሽ አጐጠጐጠ፤ ጠጒርሽ ረዘመ፤ ነገር ግን እርቃንሽን ነበርሽ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በእ​ርሻ ላይ እንደ አለ ቡቃያ አበ​ዛ​ሁሽ፤ አን​ቺም አደ​ግሽ፤ ታላ​ቅም ሆንሽ፤ በእ​ጅ​ጉም አጌ​ጥሽ፤ ከከ​ተማ ወደ ከተማ ገባሽ፤ ጡቶ​ች​ሽም አጐ​ጠ​ጐጡ፤ ጠጕ​ር​ሽም አደገ፤ ነገር ግን ዕር​ቃ​ን​ሽን ሆንሽ፤ ተራ​ቍ​ተ​ሽም ነበ​ርሽ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በእርሻ ላይ እንዳለ ቡቃያ አበዛሁሽ፥ አንቺም አደግሽ ታላቅም ሆንሽ፥ በእጅጉም አጌጥሽ፥ ጡቶችሽም አጐጠጐጡ ጠጕርሽም አደገ፥ ነገር ግን ዕርቃንሽን ሆንሽ፥ ተራቍተሽም ነበርሽ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 16:7
28 Referencias Cruzadas  

በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥


እንዲህም አለ፦ “ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፥ ጌታ ሰጠ፥ ጌታ ወሰደ፥ የጌታ ስም የተባረከ ይሁን።”


ጌታ ያዕቆብን ለራሱ፥ እስራኤልንም ግዛቱ አድርጎ መርጦታልና፥


ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም። ሃሌ ሉያ።


የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ የቅዱሳኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል። ሃሌ ሉያ።


ነገር ግን የእስራኤል ትውልዶች ፍሬያማ ነበሩ፥ እጅግም በዙ፥ ተባዙም፥ እጅግም በረቱ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች።


የእስራኤልም ልጆች ከራዓምሴስ ወደ ሱኮት በእግር ተጓዙ፤ ከሕፃናቱም ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህሉ ነበሩ።


ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር እቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።”


ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ እንደ ተወለዱ፥ በሱፍ አበባ መካከል እንደሚሰማሩ እንደ ሚዳቋ ግልገሎች ናቸው።


እኔ ቅጥር ነኝ ጡቶቼም እንደ ግንብ ናቸው፥ በዚያን ጊዜ በፊቱ ሰላምን እንደምታገኝ ሆንሁ።


እኛ ጡት የሌላት ታናሽ እኅት አለችን፥ ስለ እርሷ በሚናገሩበት ቀን ለእኅታችን ምን እናድርግላት?


አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።


በጌታ እጅ የውበት አክሊል፥ በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።


ከልብሶችሽ ጥቂቱን ወስደሽ የመስገጃ ስፍራዎችሽ ላይ በዝንጉርጉር ልብስ ያስጌጥሻቸውን መስገጆች ለራስሽ ሠራሽ በዚያም ገለሞትሽ፥ እንዲህም ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልነበረም፥ ከእንግዲህም ወዲያ አይሆንም።


በርኩሰቶችሽ ሁሉና በአመንዝራነትሽ ዕርቃንሽን ሆነሽ ተራቁተሽም በደምሽ ውስጥ ስትንፈራገጪ የነበርሽበት የልጅነትሽን ጊዜ አላስታወስሺም።


በአንቺም በኩል አለፍሁ፥ በደምሽም ውስጥ ስትንፈራገጪ አየሁሽ። በደምሽ እንዳለሽ በሕይወት ኑሪ አልሁሽ፥ አዎን በደምሽ ውስጥ እያለሽ በሕይወት ኑሪ አልሁሽ።


ወንድሞቻችሁን፦ “ዓሚ”፥ እኅቶቻችሁንም፦ “ሩሃማ” በሉአቸው።


“እግዚአብሔርም ለአብርሃም የማለለት የተስፋው ዘመን ሲቀርብ፥ ዮሴፍን የማያውቀው ሌላ ንጉሥ በግብጽ ላይ እስኪነሣ ድረስ፥ ሕዝቡ እየተጨመሩ በግብጽ በዙ።


ጌታ አምላካችሁ አብዝቶአችኋል፥ እነሆም፥ እናንተ ዛሬ እንደ ሰማይ ከዋክብት ብዛት ናችሁ።


የአባቶቻችሁ አምላክ፥ ጌታ እንደ ተናገራችሁም፥ በዚህ ቍጥር ላይ ሺህ ጊዜ እጥፍ ይጨምር፥ ይባርካችሁም።


በዓይናችሁ ፊት ዛሬ እንዳኖርኩት እንደዚህ ሕግ ሁሉ ጽድቅ የሆነች ሥርዓትና ሕግጋት ያለው ታላቅ ሕዝብስ የት ይገኛል?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos