ማሕልየ መሓልይ 5:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውዴ ብሩህና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውዴ ፍልቅልቅና ደመ ግቡ ነው፤ ከዐሥር ሺሖችም የሚልቅ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውዴ እጅግ የተዋበና ጤነኛ ነው፤ ከዐሥር ሺህ ወንዶች መካከል እርሱን የሚመስለው የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሜ ነጭና ቀይ ነው፥ ከአእላፍ የተመረጠ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውዴ ነጭና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው። |
በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ያዋን፥ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።
ስለዚህ ልኮ አስመጣው፤ እርሱም ደም ግባት ያለው፥ ዐይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበረ። ጌታም፥ “የመረጥሁት ይህ ነውና ተነሥተህ ቀባው” አለው።