La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማሕልየ መሓልይ 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል! የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ!

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኅቴ ሙሽራዬ፣ ፍቅርሽ እንዴት ደስ ያሰኛል! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛ የሚያረካ ነው፤ የሽቱሽም መዐዛ ከቅመም ሁሉ ይልቅ የቱን ያህል ይበልጥ!

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት ያስደስታል! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛል፤ የሽቶሽ መዓዛ ከማንኛውም ሽቶ ይበልጣል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ጡቶ​ችሽ እን​ዴት ያማሩ ናቸው? ጡቶ​ችሽ ከወ​ይን ይልቅ እጅግ ያማሩ ናቸው። የሽ​ቱ​ሽም መዓ​ዛው ከሽቱ ሁሉ ይልቅ እጅግ ያማረ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል! የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ!

Ver Capítulo



ማሕልየ መሓልይ 4:10
10 Referencias Cruzadas  

ንጉሡ በማዕዱ ሳለ፥ የእኔ ናርዶስ መዓዛውን ሰጠ።


መዓዛም እንደ ከርቤና እንደ ዕጣን የሆነችው፥ ከልዩ ከነጋዴ ቅመም ሁሉ የሆነችው፥ ይህች ከምድረበዳ እንደ ጢስ ምስሶ የወጣችው ማን ናት?


እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ልቤን በደስታ አሳበድሽው፥ አንድ ጊዜ በዐይኖችሽ፥ ከአንገትሽስ ድሪ በአንዱ ልቤን በደስታ አሳበድሽው።


ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፥ እጆቼ በደጁ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠባጠቡ።


ፍቅር ሆይ፥ እንዴት የተዋብሽ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ! በተድላ


የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥


ነገር ግን የሚያስፈልገኝን ሁሉ ተቀብያለሁ፤ ተትረፍርፎልኛልም፤ መዓዛው ያማረ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከኤጳፍሮዲጡስ ተቀብዬ በሁሉ ተሟልቶልኛል።


መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሳሕን ያዙ።