Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማሕልየ መሓልይ 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ልቤን በደስታ አሳበድሽው፥ አንድ ጊዜ በዐይኖችሽ፥ ከአንገትሽስ ድሪ በአንዱ ልቤን በደስታ አሳበድሽው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እኅቴ ሙሽራዬ፣ ልቤን ሰርቀሽዋል፤ በአንድ አፍታ እይታሽ፣ ከሐብልሽም በአንዱ ዕንቍ፣ ልቤን ሰርቀሽዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ፥ የዐይኖችሽ አመለካከትና የአንገትሽ ድሪ ልቤን ማርኮታል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ልቤን ማረ​ክ​ሽው፤ አንድ ጊዜ በዐ​ይ​ኖ​ችሽ፥ ከአ​ን​ገ​ት​ሽም ድሪ በአ​ንዱ፥ ልቤን ማረ​ክ​ሽው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ልቤን በደስታ አሳበድሽው፥ አንድ ጊዜ በዓይኖችሽ፥ ከአንገትሽስ ድሪ በአንዱ ልቤን በደስታ አሳበድሽው።

Ver Capítulo Copiar




ማሕልየ መሓልይ 4:9
31 Referencias Cruzadas  

እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥ የተቈለፈ ገነት፥ የታተመም ምንጭ ናት።


እንደ አንዲት ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ለማቅረብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር ቅንዐት እቀናላችኋለሁና።


እኔ የውዴ ነኝ፥ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው።


ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንዳጌጠች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።


ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ።


ጌታ አምላክሽ በመካከልሽ ኃያል ታዳጊ ነው፤ በአንቺም በፍጹም በደስታ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል።”


በአንቺ በኩል አለፍሁ፥ አየሁሽም፥ እነሆ ጊዜሽ የፍቅር ጊዜ ነበር፥ እኔም መጐናጸፊያዬን በላይሽ ላይ ዘረጋሁና ዕርቃንሽን ሸፈንሁ፥ ማልሁልሽም ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ አንቺም የእኔ ሆንሽ።


ጎልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፥ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል፤ ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።


ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዳጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።


ሳላውቅ ነፍሴ በከበረው ሠረገላ ላይ አስቀመጠችኝ።


አውከውኛልና ዐይኖችሽን ከፊቴ መልሺ፥ ጠጉርሽ ከገለዓድ እንደ ወረደ እንደ ፍየል መንጋ ነው።


እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል! የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ!


እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት፥ ውጡ፥ እናቱ በሰርጉ ቀንና በልቡ ደስታ ቀን ያደረገችለትን አክሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎሞንን እዩ።


ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፥ ዐይኖችሽም እርግቦች ናቸው።


የጉንጭሽ ውበት በከበረ ሉል፥ አንገትሽም በዕንቁ ድሪ ያማረ ነው።


በልብሶችህ ሁሉ ከርቤና ሽቱ ዝባድም አሉ፥ በዝሆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶች ይልቅ የበገናና የመሰንቆ ድምጽ ደስ ያሰኙሃል።


እንደ ሌሎቹ ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደ ኬፋም፥ አማኝ ሚስታችንን ይዘን ልንዞር መብት የለንምን?


በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ፥ እኅቴም እናቴም ነውና።”


ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት።


እርሷም ደግሞ በእውነት እኅቴ ናት፥ የእናቴ ልጅ አይደለችም እንጂ የአባቴ ልጅ ናት፥ ለእኔም ሚስት ሆነች።


ለራስህ የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ሐብል ይሆንልሃልና።


በጌጥ አስጌጥሁሽ፥ በእጅሽ ላይ አንባር በአንገትሽም ላይ ሐብል አደረግሁልሽ።


ውበትዋን በልብህ አትመኘው፥ በዐይኖችዋም አትማረክ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios