La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማሕልየ መሓልይ 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ምሰሶቹን የብር፥ መደገፊያውንም የወርቅ፥ መቀመጫውንም ሐምራዊ ግምጃ አደረገ፥ ውስጡ በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ፍቅር የተለበጠ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምሰሶዎቹን ከብር፣ መደገፊያውንም ከወርቅ ሠራ፤ መቀመጫውም በሐምራዊ ሐር የተሸፈነ ነው፤ ውስጡም በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣ ፍቅር የተለበጠ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የዙፋኑ ምሰሶዎች በብር የተለበጡ ናቸው፤ የራስ ማስደገፊያው በወርቅ ያጌጠ ነው፤ መቀመጫውም በሐምራዊ ሐር የተሸፈነ ነው፤ ውስጡ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት በፍቅር አስውበው በጠለፉት ጌጥ የተዋበ ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ምሰ​ሶ​ዎ​ቹን የብር አደ​ረገ፥ መደ​ገ​ፊ​ያ​ው​ንም የወ​ርቅ፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ሐም​ራዊ ግምጃ አደ​ረገ፤ ውስጡ ሰን​ፔር በሚ​ባል ዕንቍ የተ​ለ​በጠ ነው። ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ይልቅ እወ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ምሰሶቹን የብር፥ መደገፊያውንም የወርቅ፥ መቀመጫውንም ሐምራዊ ግምጃ አደረገ፥ ውስጡ በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ፍቅር የተለበጠ ነው።

Ver Capítulo



ማሕልየ መሓልይ 3:10
8 Referencias Cruzadas  

የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ የተከበረ ነገር ይባላል።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፥ ውብም ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።


ንጉሡ ሰሎሞን መቀመጫ ከሊባኖስ እንጨት ለራሱ አሠራ።


ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።


እንዲሁም ከታመነው ምስክር፥ ከሙታን በኩር ከሆነው፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥


ድል የሚነሣውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ዓምድ አደርገዋለሁ፤ ወደፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለትም ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን የአዲሲቱን ኢየሩሳሌምን ስም፥ እንዲሁም አዲሱን ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።