ማሕልየ መሓልይ 2:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፥ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ ውቤ ሆይ፥ ነዪ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በለስ ፍሬዋን አፈራች፤ ያበቡ ወይኖችም መዐዛቸውን ሰጡ፤ ፍቅሬ ሆይ፤ ተነሺና ነዪ፤ አንቺ የእኔ ቈንጆ፤ ከእኔ ጋራ ነዪ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በለስ ማፍራት ጀምሮአል፤ የወይን ተክልም አብቦአል፤ የአበባውም ሽታ ምድርን ሞልቶታል፤ ስለዚህ ውዴ ሆይ! ተነሺ፤ የእኔ ውብ ሆይ! ነይ አብረን እንሂድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ፥ መዓዛቸውንም ሰጡ፤ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፤ መልካምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ። በዐለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ወዳለው ጥላ ነዪ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፥ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ። |
እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ፥ አበባው ያበበ የወይንም ፍሬ ሲይዝ፥ የወይኑን ዘንግ በመግረዣ ይገርዘዋል፤ ጫፎቹንም መልምሎ ያስወግዳል።
ስለዚህ እግዚአብሔር ጥሪውን የሚያቀርበው በእኛ በኩል በመሆኑ፥ እኛ ለክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ስለ ክርስቶስ ሆነን “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ” ብለን እንለምናለን።