Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማሕልየ መሓልይ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ ውቤ ሆይ፥ ነዪ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ውዴም እንዲህ አለኝ፤ “ፍቅሬ ሆይ፤ ተነሺ፤ አንቺ የእኔ ቈንጆ፤ ከእኔ ጋራ ነዪ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ውዴ እንዲህ ይለኛል፥ ውዴ ሆይ! ተነሺ፤ የእኔ ውብ ሆይ! ነይ አብረን እንሂድ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ልጅ ወን​ድሜ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ልኝ፦ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ መል​ካ​ምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ።

Ver Capítulo Copiar




ማሕልየ መሓልይ 2:10
18 Referencias Cruzadas  

በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፥ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ ውቤ ሆይ፥ ነዪ።


መንፈሱና ሙሽራይቱም “ና!” ይላሉ። የሚሰማም “ና!” ይበል። የተጠማም ይምጣ፤ የወደደም የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድ።


እንደ አንዲት ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ለማቅረብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር ቅንዐት እቀናላችኋለሁና።


እነሆ፥ የውዴ ድምፅ! በተራሮች ላይ ሲዘልል በኮረብቶችም ላይ ሲወረወር ይመጣል።


ጌታም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ “በዘለዓለም ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ ስለዚህ በጽኑ ፍቅር ሳብሁሽ።


እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥ የውዴ ድምፅ ነው፥ እርሱም ያንኳኳል፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ፥ ራሴ በጠል፥ ጸጉሬም በሌሊት ነጠብጣብ ርሶአል።


አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን አሳየን፥ አቤቱ፥ ማዳንህንም አሳየን።


የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ዓለት እንዲህ አለኝ፦ ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፥ እግዚአብሔርንም በመፍራት የሚያስተዳድር፥


ኢየሱስም ከዚያ አልፎ ሲሄድ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው በቀረጥ መቀበያ ስፍራ ተቀምጦ አየውና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


ወዳጄ ሆይ፥ በፈርዖን ሰረገሎች እንዳለ ፈረስ መሰልሁሽ።


ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፥ ዐይኖችሽም እርግቦች ናቸው።


እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios