ሙሴ ቀደሰው፥ በቅዱሱም ዘይት ቀባው፥ ይህም ለእርሱና ለወገኖቹም ጭምር፥ እስከ ሕልፈተ ሰማይ የገባው ቃል ኪዳን ነው፥ የአምልኮውን ሥርዓት እንዲመራ፥ ካህን ሆኖም በእግዚአብሔር ስም ሕዝቡን እንዲባርክ ሥልጣን ሰጠው።
ሙሴም እጃቸውን ቀባላቸው፤ የተቀደሰውንም ዘይት ቀባው፤ ለዘለዓለሙም ሕግ ሆነው፤ ይገዙለት ዘንድ፤ ካህናትም ይሆኑት ዘንድ፤ ሕዝቡንም በስሙ ይባርኳቸው ዘንድ፤ ሰማይ ጸንቶ በሚኖርበት ዘመን ልክ ለልጆቹ ሕግ ሆናቸው።