አእምሮውን ቢስትም ራራለት፤ ጤነኛና ጠንካራ በመሆንህ እርሱን አትናቀው።
ቢያረጅ፥ አእምሮውንም ቢያጣ ለፈቃዱ እሺ በለው፥ እንደሚቻልህም አክብረው፥ በአረጀም ጊዜ አታስከፋው፥ ዋጋ በመቀበል ጊዜ አባትህን መርዳትህ አይዘነጋብህምና።