Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa መጽሐፈ ሲራክ 3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)ልጆች ለወላጆቻቸው ማድረግ ያለባቸው ግዴታ 1 ልጆች ሆይ፥ እኔን አባታችሁን ስሙኝ፥ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ እንዲህ አድርጉ፤ 2 እግዚአብሔር አባትን በልጆች ላይ አክብሯልና። የእናትንም ሥልጣን በልጆችዋ ላይ ከፍ ከፍ አድርጎአልና። 3 አባቱን የሚያከብር ልጅ ኀጢአቱ ይሰረይለታል። 4 እናቱንም የሚያከብራት ልጅ ድልብ እንደሚያደልብ ነው። 5 አባቱን የሚያከብር ልጅ በልጆቹ ደስ ይለዋል፤ በሚጸልይበትም ቀን ፈጣሪው ይሰማዋል። 6 አባቱን የሚያከብር ልጅ ዕድሜው ይረዝምለታል። 7 እግዚአብሔርን የሚሰማ ልጅ እናቱን ያሳርፋታል። 8 እንደ አገልጋዮቹም ለወላጁ ይገዛል። 9 በረከቱ ትደርስህ ዘንድ በቃልህም በሥራህም አባትህን አክብረው። 10 የአባት በረከት የልጅን ቤት ያጸናልና፥ የእናት ርግማን ግን መሠረትን ይነቅላል። 11 አባትህን በማቃለል አትመካ፤ አባትህን ማቃለል ትምክሕት አይሆንህምና ሰው በአባቱ ክብር ይከብራል፤ የሰውም ውርደቱ እናቱን በማቃለሉ ነው። 12 ልጄ ሆይ፥ በእርጅናው ጊዜ አባትህን ርዳው፥ በሕይወቱም ሳለ አታሳዝነው። 13 ቢያረጅ፥ አእምሮውንም ቢያጣ ለፈቃዱ እሺ በለው፥ እንደሚቻልህም አክብረው፥ በአረጀም ጊዜ አታስከፋው፥ ዋጋ በመቀበል ጊዜ አባትህን መርዳትህ አይዘነጋብህምና። 14 ስለ ኀጢአትም ፋንታ ጽድቅ ትሠራልሃለች። 15 በመከራህም ቀን ይታሰብልሃል፤ ፀሐይ በረድን እንደሚያቀልጠው ኀጢአቶችህ እንደዚሁ ይቀልጣሉ። 16 አባቱን የሚጥል ሰው እግዚአብሔርን እንደሚፀርፍ ነው፤ እናቱን የሚያሳዝናትም በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነው። ስለ ትሕትና 17 ልጄ ሆይ፥ ሥራህ በሃይማኖትህ ይገለጥ፤ እውነተኞች ሰዎችም ይወድዱሃል። 18 እንደ ገናንነትህ መጠን እንደዚሁ ራስህን አዋርድ። በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋህን ታገኛለህ። 19 የእግዚአብሔር ሥራው ታላቅ ነውና፥ በቅዱሳንና በትሑታን ዘንድ ይመሰገናል። 20 የሚበረታብህን አትፈልግ፤ የማትችለውንም አትመርምር፤ 21 ነገር ግን የታዘዝኸውን ዐስብ። በስውር ያለው ግን አያስጨንቅህ። 22 አላስፈላጊ ሥራዎችን አትመራመር፤ ከሰዎች ይልቅ ለአንተ እጅግ ተገልጦልሃልና። 23 ብዙ ሰዎችን መታበያቸው አሳታቸው። ብዙ ሰዎችንም የልቡናቸው ትዕቢት ጣላቸው። 24 ጥፋትን የሚወዳት በእርሷ ይሞታል፥ ክፉ ልቡናም በመጨረሻው ይታመማል። 25 ክፉ ልቡና በመከራ ይገረፋል፤ ኀጢአተኛ ሰውም በኀጢአቱ ላይ ኀጢአትን ይጨምራል። 26 ለትዕቢተኞች ጥፋት ፈውስ የላትም፤ ክፉ ተክል በውስጣቸው ሥር ሰድዶአልና። 27 የብልህ ሰው ልቡና ምሳሌን ይተረጕማል፤ የዐዋቂ ሰው ጆሮም ጥበብ መስማትን ትወዳለች። ስለ ምጽዋት 28 የምትነድድ እሳትን ውኃ ያጠፋታል። ምጽዋትም ኀጢአትን ታስተሰርያለች። 29 ምጽዋትን ለሚሰጥ ሰው በመጨረሻ ይታሰብለታል፤ በሚሰነካከልበትም ጊዜ መጠጊያን ያገኛል። |