ሮሜ 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአብርሃም ዘር ስለ ሆኑ ሁሉም የእርሱ ልጆች ናቸው ማለት አይደለም፤ ነገር ግን “ዘርህ በይስሐቅ ይጠራልሃል፤” ተባለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአብርሃም ዘርም ስለ ሆኑ፣ ሁሉም ልጆቹ አይደሉም፤ ይልቁንስ፣ “ዘርህ በይሥሐቅ በኩል ይጠራልሃል” እንደ ተባለው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የአብርሃም ዘር ሁሉ የአብርሃም ልጆች ናቸው ማለት አይደለም። እግዚአብሔር አብርሃምን “ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ ነው” ስላለው ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአብርሃም ዘር ሁሉ ልጆቹ የሆኑት አይደለም፤ ከይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል አለው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን፦ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል ተባለ። |
እንግዲህ ለንስሓ የሚገቡ ፍሬዎች አፍሩ፤ በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን፤’ አትበሉ፤ ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር እንደሚችል እነግራችኋለሁና።