ሮሜ 9:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሆሴዕ ደግሞ እንዲህ እንደሚል፤ “ሕዝቤ ያልሆነውን ‘ሕዝቤ’ ብዬ፥ ያልተወደደችውንም ‘የተወደደችው’ ብዬ እጠራለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሆሴዕ እንዲህ እንደሚል፤ “ሕዝቤ ያልሆኑትን፣ ‘ሕዝቤ’ ብዬ፣ ያልተወደደችውንም፣ ‘የተወደደች’ ብዬ እጠራለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም በነቢዩ በሆሴዕ እንዲህ እንደ ተባለ ነው፦ “የእኔ ሕዝብ ያልነበረውን ‘ሕዝቤ!’ ብዬ እጠራዋለሁ፤ ያልተወደደውንም ሕዝብ ‘የተወደደ!’ ብዬ እጠራዋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢዩ ሆሴዕ እንዲህ እንዳለ “ወገኔ ያልነበረውን ወገኔ አደርገዋለሁ፤ ወዳጄ ያልነበረችውንም ወዳጄ አደርጋታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ደግሞ በሆሴዕ፦ ሕዝቤ ያልሆነውን ሕዝቤ ብዬ፥ ያልተወደደችውንም የተወደደችው ብዬ እጠራለሁ፤ |
በአንቺ በኩል አለፍሁ፥ አየሁሽም፥ እነሆ ጊዜሽ የፍቅር ጊዜ ነበር፥ እኔም መጐናጸፊያዬን በላይሽ ላይ ዘረጋሁና ዕርቃንሽን ሸፈንሁ፥ ማልሁልሽም ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ አንቺም የእኔ ሆንሽ።
በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁ፥ በሮሜ ላላችሁ ሁሉ፥ ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
ቀድሞ የእርሱ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ ቀድሞ ምሕረትን አላገኛችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።