Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 7:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ሕዝብህን እስራኤልን ለዘለዓለም ያንተው የራስህ ሕዝብ አድርገህ አጽንተኸዋል፤ ጌታ ሆይ፤ አንተም አምላክ ሆነኸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ሕዝብህን እስራኤልን ለዘላለም የራስህ ሕዝብ አድርገህ አጽንተኸዋል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተም አምላክ ሆነኸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እስራኤልንም ለዘለዓለም ሕዝብህ አደረግህ፤ ጌታ ሆይ፥ አንተም አምላካቸው ሆንክ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ሕዝ​ብ​ህ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕዝብ አድ​ር​ገህ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ኸ​ዋል፤ አን​ተም፥ አቤቱ፥ አም​ላክ ሆነ​ሃ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘላለም ሕዝብ አድርገህ አጽንተኸዋል፥ አንተም፥ አቤቱ፥ አምላክ ሆነሃቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 7:24
20 Referencias Cruzadas  

ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት አንተ ሕዝቡና ርስቱ መሆንህን፥ ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቅ ዛሬ ተናግሮአል፤


ቀድሞ የእርሱ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ ቀድሞ ምሕረትን አላገኛችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።


ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑ ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የሚሆኑበትን ሥልጣን ሰጣቸው፤


ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


እነሆ፤ ጌታ መዳኛዬ ነው፤ እታመናለሁ፤ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ የመዳኔ ምክንያትም ሆኖአል።”


በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥ ቅጥሮችዋን መርምሩ፥ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።


ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።


አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።


እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።


በዚያን ዘመን፥ ይላል ጌታ፥ ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘለዓለም ሕዝብህ አደረግኸው፤ አንተም፥ አቤቱ፥ አምላክ ሆነኸዋል።


ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፥ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፥ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክቶቻቸውን ከፊቱ አሳዶ ታላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ?


ሙሴና ሌዋውያን ካህናትም ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ አሉ፦ “እስራኤል ሆይ፥ ዝም ብለህ አድምጥ! አንተ ዛሬ የጌታ እግዚአብሔር ሕዝብ ሆነሃል።


ጌታ ኃይሌና መዝሙሬ ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነዋለሁም፥ የአባቴ አምላክ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።


ለእኔ ሕዝብ አድርጌ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብጽ ጭቆና ያወጣኋችሁ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”


አንተ የማታስተውልና ኀሊና ቢስ ሕዝብ፥ ለጌታ ምላሽህ እንዲህ ነው? እርሱ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህና የሠራህ ያጸናህም እርሱ አይደለምን?”


አሁንም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአገልጋይህና ለቤቱ የሰጠኸውን ተስፋ ለዘለዓለም ጠብቅለት፤ እንደተናገርኸውም ፈጽም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios