ሮሜ 9:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንድ ዓይነት ጭቃ አንዱን ዕቃ ለክብር፥ አንዱን ደግሞ ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ መብት የለውምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሸክላ ሠሪ፣ ከሚሠራው ጭቃ፣ አንዳንዱን ሸክላ ለከበረ፣ ሌሎቹን ደግሞ ለተራ አገልግሎት የማድረግ መብት የለውምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሸክላ ሠሪ ከአንድ ዐይነት የሸክላ ጭቃ አንዱን ዕቃ ለክብር፥ ሌላውን ለተራ አገልግሎት አድርጎ ለመሥራት ሥልጣን የለውምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሸክላ ሠሪ ከአንድ ጭቃ ግማሹን ለክብር፥ ግማሹንም ለኀሳር አድርጎ ዕቃን ሊሠራ አይችልምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን? |
መጥረቢያ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፤ ዘንግም ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኩራራ ነው።
ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን?
በውኑ ይህ ሰው ኢኮንያን የተናቀና የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ነውን? ወይስ እርሱ ማንም የማይፈልገው የሸክላ ዕቃ ነውን? እርሱና ዘሩስ በማያውቋት ምድር ስለምን ተወርውረው ተጣሉ?
ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን?