ጠባቂውም፥ “የመጀመሪያው ሰው ሩጫ የሳዶቅን ልጅ የአሒማዓጽን ሩጫ ይመስለኛል” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፤ ቢመጣም የምሥራች ይዞ ነው” አለ።
ሮሜ 5:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ጻድቅ ሰው ሲል የሚሞት ሰው ማግኘት አስቸጋሪ ነው፤ ስለ መልካም ሰው ሲል ሊሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጻድቅ የሚሞት ሰው ማግኘት እጅጉን ያዳግታል፤ ለደግ ሰው ሲል ሊሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጻድቅ ምትክ ሆኖ የሚሞት ሰው ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው፤ ሆኖም በደግ ሰው ምትክ ለመሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ክፉዎች በጭንቅ ጊዜ ስንኳ ቢሆን ሊሞት የሚደፍር አይገኝም፤ ስለ ደጋጉ ግን ሊሞት የሚጨክን የሚገኝ እንዳለ እንጃ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። |
ጠባቂውም፥ “የመጀመሪያው ሰው ሩጫ የሳዶቅን ልጅ የአሒማዓጽን ሩጫ ይመስለኛል” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፤ ቢመጣም የምሥራች ይዞ ነው” አለ።
ሰዎቹ ግን፥ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ ግማሾቻችን እንኳ ብንሞት፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ አንተ ግን ብቻህን ከእኛ ከዐሥሩ ሺህ ትበልጣለህ! ስለዚህ በከተማ ሆነህ ብትረዳን ይሻላል” አሉት።
በዓይናቸው አይተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ተመልሰው እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፥ ጆሮአቸው ደንቁሮአል፥ ዓይናቸውም ተጨፍኖአል፤
እነርሱም ስለ እኔ ነፍስ ሲሉ አንገታቸውን አደጋ ላይ ጣሉ፤ እነርሱንም እኔ ብቻ ሳልሆን የአሕዛብም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰግኗቸዋል፤