La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሮሜ 5:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚህ ብቻ ሳይሆን፥ መከራ ጽናትን እንደሚያስገኝ ስለምናውቅ በመከራም ጭምር እንመካለን፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራችንም ሐሤት እናደርጋለን፤ ምክንያቱም መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ብቻ ሳይሆን መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝልን ስለምናውቅ በመከራችንም እንመካለን።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የም​ን​መካ በእ​ር​ስዋ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በመ​ከ​ራ​ችን ደግሞ እን​መ​ካ​ለን እንጂ፤ መከራ በእና ላይ ትዕ​ግ​ሥ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​መጣ እና​ው​ቃ​ለ​ንና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤

Ver Capítulo



ሮሜ 5:3
21 Referencias Cruzadas  

እኔ ግን በጌታ ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።


በመታገሣችሁም ነፍሳችሁን ታተርፋላችሁ።


እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቆጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤


ይህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።


ፍጥረት ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን እኛ ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት በናፍቆት እየተጠባበቅን እኛ ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።


ይህ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ርብቃ ደግሞ ከአንድ ሰው ከአባታችን ከይስሐቅ በፀነሰች ጊዜ፥


ቀላል የሆነው ጊዜያዊ መከራችን ከመመዘኛዎች ሁሉ ለሚያልፈው ለዘላለማዊ ክብር ያዘጋጀናል።


ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የጌታን የራሱን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግለው በዚህ የቸርነት ሥራ ከእኛ ጋር አብሮን እንዲሄድ በአብያተ ክርስቲያናት ተመርጧል።


ስለዚህ፥ ክብራችሁ ነውና፥ ስለ እናንተ ስለምቀበለው መከራዬ እንዳትታክቱ እለምናችኋለሁ።


ስለ ሆነም በክርስቶስ የምታምኑ ብቻ ሳትሆኑ ስለ እርሱ መከራንም ደግሞ የምትቀበሉ ትሆናላችሁ፤ ይህም ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤


ጌታ ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ተፈትኖ ይቀበላልና፥ በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው።


ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ ብፁዓን ናችሁ። ዛቻቸውንም አትፍሩ፤ አትታወኩም።