ሮሜ 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳይገረዝም በእምነቱ ባገኘው የጽድቅ ማኅተም፥ መገረዝን እንደ ምልክት ተቀበለ፤ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ፥ ለእነርሱም ጽድቅ ሆኖ እንዲቆጠርላቸው አባት ነውና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳይገረዝ በነበረው እምነት ላገኘው ጽድቅ፣ የመገረዝን ምልክት ይኸውም የጽድቅን ማኅተም ተቀበለ፤ ስለዚህ ለሚያምኑ ነገር ግን ላልተገረዙት ጽድቅ ይቈጠርላቸው ዘንድ የሁሉ አባት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃም ገና ከመገረዙ በፊት እምነቱ ጽድቅ ሆኖ እንደ ተቈጠረለት ማረጋገጫ ምልክት እንዲሆነው ተገረዘ፤ ስለዚህ አብርሃም፥ ሳይገረዙ ለሚያምኑና እምነታቸው ጽድቅ ሆኖ ለሚቈጠርላቸው ሁሉ አባት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳይገዘር እግዚአብሔር አብርሃምን በእምነት እንደ አጸደቀው በእርሱ ላይ ይታወቅ ዘንድ ግዝረትን የጽድቅ ማኅተም ትሆነው ዘንድ ምልክት አድርጎ ሰጠው። ሳይገዘሩ ለሚያምኑ ሁሉ አባት ሊሆን፥ አብርሃም በእምነት እንደ ከበረ እነርሱም በእምነት እንደሚከብሩ ያውቁ ዘንድ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳይገረዝም በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም የሆነ የመገረዝን ምልክት ተቀበለ፤ ይህም እነርሱ ደግሞ ጻድቃን ሆነው ይቆጠሩ ዘንድ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ አባት እንዲሆን ነው፥ |
ደሙም በምትኖሩባቸው ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብጽን ምድር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም።
“አንተ ግን ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሰንበቶቼን ፈጽሞ ጠብቁ፥ ይህ የምቀድሳችሁ ጌታ እኔ እንደሆንሁ እንድታውቁ በእኔና በእናንተ መካከል ለትውልዶቻችሁ ምልክት ነውና።
በእኔና በእስራኤል ልጆች መካከል የዘለዓለም ምልክት ነው፤ ጌታ ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ፈጥሮአልና፥ በሰባተኛውም ቀን ከሥራው አርፎአልና፥ ተነቃቅቶአልና።’”
እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል ሰምታችሁ፥ በክርስቶስም አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤
ጌታ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ እንድትወደው፥ በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህ ጌታ የአንተንና የዘርህን ልብ ይገርዛል።
በክርስቶስም በማመን በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ እንጂ በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴ ጽድቅ ሳይኖረኝ፥ በእርሱ እንድገኝ ነው፤
ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር አቻ የሆነ ክቡር እምነትን ላገኙ፤
የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተነገራቸው።