ሮሜ 3:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም በሕግ ሥራ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት አይጸድቅም፤ በሕግ አማካኝነት ኃጢአት ይታወቃልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ማንም ሥጋ ለባሽ በርሱ ፊት ሊጸድቅ አይችልም፤ ይልቁንም በሕግ አማካይነት ኀጢአትን እንገነዘባለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት፥ ሕግን በመፈጸም አይጸድቅም፤ ሕግ የሚያሳየው ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኦሪት የተነሣ ኀጢአት ስለ ታወቀች ሰው ሁሉ የኦሪትን ሥርዐት በመፈጸም በእግዚአብሔር ፊት አይጸድቅም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና። |
ሆኖም ሰው የሚጸድቀው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ በሕግ ሥራ እንዳልሆነ አውቀን፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ በማመን እንድንጸድቅ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። ሥጋ ሁሉ በሕግ ሥራ አይጸድቅም።