ሮሜ 2:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚፈፅሙት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙት አይጸድቁምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን የሚባሉት ለሕጉ የሚታዘዙ እንጂ፣ ሕጉን የሚሰሙ አይደሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቁ ሕጉን ሰምተው በሥራ ላይ የሚያውሉት ናቸው እንጂ ሕጉን ሰምተው በሥራ ላይ የማያውሉት አይደሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚያደርጉ ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ አይጸድቁምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚያደርጉት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ ጻድቃን አይደሉምና። |
ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህን ቃላት ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ተናገር፥ እንዲህም በል፦ የዚህን ቃል ኪዳን ቃላት ስሙ አድርጉትም።
ከዚያኛው ይልቅ ይህ ሰው ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ እላችኋለሁ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላልና፥ ራሱን ግን ዝቅ የሚያደርግ ከፍ ይላል።”
ሆኖም ሰው የሚጸድቀው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ በሕግ ሥራ እንዳልሆነ አውቀን፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ በማመን እንድንጸድቅ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። ሥጋ ሁሉ በሕግ ሥራ አይጸድቅም።
“አሁንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው በሕይወትም እንድትኖሩ፥ የአባቶቻችሁም አምላክ ጌታ ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ የማስተምራችሁን ሥርዓትና ሕግጋት ስሙ።
ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአት በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሕግና ሥርዓት ስሙ።
እንግዲህ፥ እስራኤል ሆይ፥ ስማ! መልካም እንዲሆንልህ፥ የአባቶችህም አምላክ ጌታ እንደ ተናገረ፥ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር፥ እጅግ እንድትበዛ በጥንቃቄ ጠብቅ።
በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ያልረከሰ አምልኮ፥ “አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች፥ እንዲሁም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳት፥ ራስንም ከዓለም ርኲሰት መጠበቅ ነው።”