La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሮሜ 15:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኛ ብርቱዎች የሆንን የደካሞችን ድካም መሸከም እንጂ ራሳችንን ማስደሰት የለብንም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኛ ብርቱዎች የሆንን፣ የደካሞችን ጕድለት መሸከም እንጂ ራሳችንን ማስደሰት የለብንም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኛ በእምነት ብርቱዎች የሆንን፥ የደካሞችን ድካም መሸከም ይገባናል እንጂ ራሳችንን ብቻ የምናስደስት መሆን የለብንም፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሚ​ገ​ባስ እና ብር​ቱ​ዎች ደካ​ሞ​ችን በድ​ካ​ማ​ቸው እን​ድ​ን​ረ​ዳ​ቸው ነው፤ ለራ​ሳ​ች​ንም አና​ድላ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኛም ኃይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንድንሸከም ራሳችንንም ደስ እንዳናሰኝ ይገባናል።

Ver Capítulo



ሮሜ 15:1
13 Referencias Cruzadas  

በእምነት የደከመውንም አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሳትፈርዱበት ተቀበሉት።


ሁሉን መብላት እንደሚችል የሚያምን አለ፤ በእምነት ደካማው ግን አትክልት ይበላል።


ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ በእምነት በረታ እንጂ፤ እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ አልተጠራጠረም።


እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን።


ደካሞችን መጥቀም እንድችል ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንኩ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን ማዳን እንድችል፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።


ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም፥ በመንገላታት፥ በችግር፥ በስደት፥ በጭንቀት፥ ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያንጊዜ እበረታለሁ።


በተረፈ በጌታ በኃይሉ ብርታትም ጠንክሩ።


እያንዳንዱም ሰው የራሱን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌላውንም ሰው ጥቅም ያስብ።


ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ሰነፎችን ገሥጹ፤ ፈሪዎችን አጽኑ፤ ደካሞችን እርዱ፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።


እንግዲህ ልጄ ሆይ! አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።


ልጆች ሆይ፥ አብን አውቃችሁታልና ጽፌላችኋለሁ። አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችሁታልና ጽፌላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በውስጣችሁ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ ጽፌላችኋለሁ።