ራእይ 8:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ለግማሽ ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጉ ሰባተኛውን ማኅተም በፈታ ጊዜ፣ ግማሽ ሰዓት ያህል በሰማይ ዝምታ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጉ ሰባተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ እኩል ሰዓት ያኽል በሰማይ ዝምታ ሆነ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ግማሽ ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ። |
እነሆ፥ እጄን በላያቸው ላይ አነሣለሁ፥ በምርኮ ተገዝተውላቸው ለነበሩት ራሳቸው በምርኮ ይዘረፋሉ፤ የሠራዊት ጌታም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።
ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጉር ጥቁር ሆነች፤ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነች፤
ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ “ና” ሲል ሰማሁ። አየሁም፤ እነሆም ጥቁር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።