ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት አመንዝራ እንደ ሆነች ተመልከቱ! ቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፤ ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤ አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ማደሪያ ሆነች!
ራእይ 17:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ና፤ በብዙም ውሃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን አመንዝራ ሴት ፍርድ አሳይሃለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ እንዲህ አለኝ፤ “ና፤ በብዙ ውሆች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን አመንዝራ ፍርድ አሳይሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰባቱን ጽዋዎች ይዘው ከነበሩት ከሰባቱ መላእክት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ አለኝ፦ “ና! በብዙ ውሃዎች ላይ በተቀመጠችው በታላቂቱ አመንዝራ ሴት ላይ የሚደርሰውን ፍርድ አሳይሃለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ና፤ በብዙም ውሃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፦ ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤ |
ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት አመንዝራ እንደ ሆነች ተመልከቱ! ቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፤ ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤ አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ማደሪያ ሆነች!
“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብረሻል እስራትሽንም በጥሰሻል፤ አንቺም፦ ‘አላገለግልም’ አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ ይህ ነው፤ መልአኩንም ልኮ ራእዩን ለአገልጋዩ ለዮሐንስ ገለጠ፤
ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቁጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።
ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። የብርቱ ቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ እንዲሰጣትም ታላቂቱ ባቢሎን በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።
ሰባቱ የመጨረሻዎቹ መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ወደዚህ ና፤ የበጉን ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ፤” ብሎ ተናገረኝ።
ከዚያ በኋላም አየሁ፤ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ! እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ “ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ መሆን ያለበትን ነገር አሳይሃለሁ፤” አለ።