La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 97:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ጠላቶቹንም በዙሪያው ያቃጥላል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እሳት በፊቱ ይሄዳል፤ በዙሪያው ያሉትንም ጠላቶቹን ይፈጃል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እሳት እፊት እፊቱ ይሄዳል፤ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ያቃጥላል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለያ​ዕ​ቆብ ይቅ​ር​ታ​ውን ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት እው​ነ​ቱን አሰበ፤ የም​ድር ዳር​ቻ​ዎች ሁሉ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ማዳን እዩ።

Ver Capítulo



መዝሙር 97:3
19 Referencias Cruzadas  

ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ ተናጉም እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና።


ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፥ ከአፉም የሚበላ እሳት ነደደ፥ ፍምም ከእርሱ በራ።


አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፥ እሳት በፊቱ ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ ነፋስ አለ።


እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስ መጣ፥ በዙሪያው ብርሃን ያለው መብረቅን የሚረጭ ታላቅ ደመና ነበር፥ በእሳቱም መካከል የሚያንጸባርቅ ነገር ነበረ።


ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ መቅሠፍትም ከእግሩ ይወጣል።


“እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ ሥርንና ቅርንጫፍንም አያስቀርላቸውም።


እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለች፤ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረትም ታነድዳለች።’”


እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፥ እስከ ሰማይም ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፥ ጨለማም ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ።


ያስተምራችሁ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፥ በምድርም ላይ ታላቁን እሳቱን አሳያችሁ፥ ከእሳቱም መካከል የእርሱን ድምፅ ሰማችሁ።።


በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ጌታ ፊት ለፊት አናገራችሁ።


ነገር ግን እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤


አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።


ማንም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል፤ ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል።


በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ሁሉ በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።