እኔ ከታናሽነቴ ችግረኛ ለሞትም የቀረብሁ ነኝ፥ በአስደንጋጭ ነገሮችህ ተሰቃየሁ፤ ምንም አቅም የለኝም።
ቍጣህ በላዬ ላይ ተከነበለ፤ መዓትህም አጠፋኝ።
ብርቱ ቊጣህ አደቀቀኝ፤ አስፈሪው ቅጣትህ ያጠፋኛል።
በስምህ ቀኑን ሁሉ ደስ ይላቸዋል፥ በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ፤
ድንጋጤ በላዬ ተመለሰብኝ፥ ክብሬንም እንደ ነፋስ ያሳድዱታል፥ ብልጽግናዬም እንደ ደመና አልፋለች።”
አመድን እንደ እህል ቅሜአለሁና፥ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና፥
ሥጋዬ አንተን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፥ ከፍርድህ የተነሣ ፈርቻለሁ።
ዕድሜውንም አሳጠርህ፥ በእፍረትም ሸፈንኸው።
የቁጣህን ጽናት ማን ያውቃል? የቁጣህንስ ግርማ ማን ያውቃል?
እኛ በቁጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና።
በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው እርሱ፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ፥ ከሕግ እርግማን ዋጅቶናል፤ “በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው፤” ተብሎ ተጽፎአልና
ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፤ ማንስ ጸንቶ ሊቆም ይችላል?” አሉአቸው።