በመቃብርስ ውስጥ ጽኑ ፍቅርህን፥ እውነትህንስ በጥፋት ስፍራ ይነገራሉን?
ድንቅ ሥራህ በጨለማ ስፍራ፣ ጽድቅህስ በመረሳት ምድር ትታወቃለችን?
ተአምራትህ በጨለማ ስፍራ ይታወቃሉን? ታዳጊነትህስ በተረሱ ሰዎች አገር ይታያልን?
ባሕርንና መስዕን አንተ ፈጠርህ፤ ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል። ስምህንም ያመሰግናሉ።
ጠላት ነፍሴን አሳድዶአታል፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ አጐስቁሎአታል፥ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኑሮኛል።
በጠላቶቼ ዘንድ ተነወርኹ፥ ይልቁንም በጎረቤቶቼ ዘንድ፥ ለሚያውቁኝም ፍርሃት ሆንሁ፥ በሜዳ ያዩኝም ከእኔ ሸሹ።
ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተቈጠርሁ፥ ረዳትም እንደሌለው ሰው ሆንሁ።
በሚመጣው ዘመን ነገር ሁሉ የተረሳ ይሆናልና ለዘለዓለም የሚሆን የጠቢብና የአላዋቂ መታሰቢያ አይገኝም። አዬ ጉድ! ጠቢብ ከአላዋቂ ጋር እንዴት ይሞታል!
እንዲሁም ክፉዎች ተቀብረው አየሁ፥ ነገር ግን ቅን አድራጊዎች ከቅድስት ስፍራ ወጡ፥ በከተማይቱም ውስጥ ተረሱ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።
ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፥ ሙታን ግን አንዳችም ነገር አያውቁም፥ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚያ በኋላ ዋጋ የላቸውም።
ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታሉ፤ የሚያዩትም ጭንቀት፤ ጨለማና የሚያስፈራም ጭጋግ ብቻ ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ።
የመንግሥቱ ልጆች ግን ውጪ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”
የገዛ ነውራቸውን አረፋ የሚደፍቁ እየባሰ የሚሄድ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም የተዘጋጀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።