መዝሙር 84:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወፍ ለእርሷ ቤትን አገኘች፥ ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች፥ በመሠውያህ አጠገብ፥ የሠራዊት አምላክ ንጉሤም አምላኬም ሆይ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብፁዓን ናቸው፤ በቤትህ የሚኖሩ፣ እነርሱም ለዘላለም ያመሰግኑሃል። ሴላ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘወትር የምስጋና መዝሙር ለአንተ እያቀረቡ በመቅደስህ የሚኖሩ እንዴት የተባረኩ ናቸው! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችንና መድኀኒታችን ሆይ፥ መልሰን፥ ቍጣህንም ከእኛ መልስ። |
ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥ ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፥ በዓል የሚያከብሩ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።
ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ይቆማሉ፤ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ውስጥ ያመልኩታል፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ድንኳኑን በእነርሱ ላይ ይዘረጋል።