በፊትዋም ስፍራን አዘጋጀህ፥ ሥሮችዋንም ተከልህ ምድርንም ሞላች።
ተራሮች በጥላዋ ተሸፈኑ፤ ግዙፍ ዝግቦችም በቅርንጫፎቿ ተጠለሉ።
ጥላዋ ተራራዎችን የቅርንጫፎችዋም ጥላ የሊባኖስ ዛፎችን ሸፈነ።
ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤ አፍህን አስፋ፥ እሞላዋለሁም።
የጌታ ዛፎች እርሱም የተከላቸው የሊባኖስ ዝግባዎች ይጠግባሉ።
በሰይፍህም በቀሥትህም ሳይሆን በፊታችሁም ተርብ ሰድጄ ሁለቱን የአሞራውያንን ነገሥታት ከፊታችሁ አሳደዳቸው።