የጌታን ሥራ አስታወስሁ፥ የቀደመውን ተኣምራትህን አስታወሳለሁና፥
ሥራህን ሁሉ አሰላስላለሁ፤ ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ።
ሥራዎችህን በጥሞና አሰላስላለሁ፤ ለድርጊቶችህም ከፍ ያለ ግምት እሰጣለሁ።
በግብጽ ሀገርና በጣኔዎስ በረሃ በአባቶቻቸው ፊት የሠራውን ተአምራት።
ቃሌ ለእርሱ ይጣፍጠው፥ እኔም በጌታ ደስ ይለኛል።
ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።
አገልጋዮቹ የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራውን ድንቅ ሥር አስቡ፥ ተአምራቱን የተናገረውንም ፍርድ።
ከጥንት የነበረውን ፍርድህን አሰብሁ፥ አቤቱ፥ ተጽናናሁም።
የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፥ የእጅህንም ሥራ አስተዋልሁ።
የመንግሥትህን ክብር ይናገራሉ፥ ኃይልህንም ይነጋገራሉ፥
ትውልደ ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፥ ኃይልህንም ያወራሉ።
ጉዳቴን የሚሹ ባፈሩና በተነወሩ ጊዜ አንደበቴ ደግሞ ሁልጊዜ ጽድቅህን ይናገራል።
እርሱም የቀደመውን ዘመን እንዲህ ብሎ አሰበ፦ የበጎቹን እረኛ ከባሕሩ ያወጣው ወዴት ነው ያለው? ቅዱስ መንፈሱንም በመካከላቸው ያኖረ ወዴት ነው ያለው?
ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም ሆነ፥ ስትነሣም ንገራቸው።
ልትፈራቸው አይገባም፥ ነገር ግን ጌታ አምላካችሁ በፈረዖንና በግብጽ ሁሉ ያደረገውን አስብ፥
ዓይንህ ያየችውን ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ ጌታ አምላክህ ሲያስወጣህ የጸናችውን እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ፥ እንደዚሁ ሁሉ ጌታ አምላክህ አንተ በምትፈራቸው በሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደርጋል።