ውሃውንም በኤልያስ ካባ መትቶ፥ “የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው?” አለ፤ ከዚያም በኋላ እንደገና በመታው ጊዜ ውሃው ወደ ቀኝና ወደ ግራ ተከፍሎለት ወደ ማዶ ተሻገረ፤
መዝሙር 74:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ምንጮቹንና ፈሳሾቹን ሰነጠቅህ፥ አንተ ሁልጊዜ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንጮችንና ፈሳሾችን ያፈለቅህ አንተ ነህ፤ ሳያቋርጡ የሚፈስሱትንም ወንዞች አደረቅህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንጮችና ጅረቶች እንዲፈስሱ አደረግህ፤ ታላላቅ ወንዞችን ግን አደረቅህ። |
ውሃውንም በኤልያስ ካባ መትቶ፥ “የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው?” አለ፤ ከዚያም በኋላ እንደገና በመታው ጊዜ ውሃው ወደ ቀኝና ወደ ግራ ተከፍሎለት ወደ ማዶ ተሻገረ፤
ከዚህ በኋላ ኤልያስ ካባውን አውልቆ በመጠቅለል ውሃውን መታው፤ ውሃውም ወደ ቀኝና ወደ ግራ ተከፍሎላቸው ኤልያስና ኤልሳዕ በደረቅ ምድር ተሻገሩ፤
ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ ጌታ የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።
ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።