La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 69:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ መቆሚያም የለኝም። ወደ ጥልቅ ባሕር ገባሁ ማዕበልም አሰጠመኝ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በጩኸት ደከምሁ፤ ጕረሮዬም ደረቀ፤ አምላኬን በመጠባበቅ፣ ዐይኖቼ ፈዘዙ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከመጮኼ ብዛት የተነሣ ደከምኩ፤ ጒሮሮዬም ቈሰለ፤ አምላኬን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እሰይ! እሰይ! የሚ​ሉኝ አፍ​ረው ወዲ​ያው ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ።

Ver Capítulo



መዝሙር 69:3
18 Referencias Cruzadas  

የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለች፥ የሚሸሹበትንም ያጣሉ፥ ተስፋቸውም ነፍስን አሳልፎ መስጠት ነው።”


ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፥ የሞት ጥላ በዐይኖቼ ቆብ ላይ አለ፥


ዐይኖቼ ለማዳንህ፥ ለጽድቅህም ቃል ፈዘዙ።


መቼ ታጽናናኛለህ እያልሁ ዐይኖቼ ስለ ቃልህ ፈዘዙ።


እንደ ውኃ ፈሰስሁ፥ አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ፥ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፥ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ።


አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ለምን ራቅህ?


አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና ፍጽምናና ቅንነት ይጠብቁኝ።


በእውነት ሰው እንደ ጥላ ይመላለሳል፥ በእውነት በከንቱ ይታወካል። ያከማቻል የሚሰበስብለትንም አያውቅም።


ከጥፋት ጉድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።


በሞት የሚያስታውስህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?


ስድብ እስክታመም ድረስ ልቤን ሰበረው፥ አስተዛዛኝም ተመኘሁ አላገኘሁም፥ የሚያጽናናኝም አጣሁ።


በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታችኛው ጉድጓድ አስቀመጥኸኝ።


እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፥ እንደ ርግብም አጉረመረምሁ፤ ዐይኖቼ ወደ ላይ በማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፥ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ።


ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማይቱ ጐዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዓይኔ በእንባ ደከመች፥ አንጀቴም ታወከ፥ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ጉበቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከወዲሁ ሁሉ ነገር እንደ ተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉም ቃል ይፈጸም ዘንድ “ተጠማሁ” አለ።


ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ ነገር ግን ምንም ለማድረግ አትችልም፤ ከዛሬ ነገ ይመጣሉ በማለትም ዐይኖችህ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ።


እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤