ጌታ እንዲህ አለ፦ ከባሳን አመጣቸዋለሁ፥ ከባሕርም ጥልቅ እመልሳቸዋለሁ፥
እግርህ በጠላትህ ደም ውስጥ እንዲጠልቅ፣ የውሻህም ምላስ ከጠላትህ ድርሻውን እንዲያገኝ ነው።”
አንተ ደማቸውን ረግጠህ ታልፋለህ፤ ውሾችህም ደም ይልሳሉ።”
ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥ ጀርባቸውም ዘወትር ይጉበጥ።
እነዚህም የአውራጆች አለቆች ጉልማሶች ከከተማይቱ ወጡ፤ ሠራዊትም ተከተላቸው።
ሠረገላውም በሰማርያ ኲሬ ታጠበ፤ ጌታም አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ደሙን ውሾች ላሱት፤ በዚያም ኲሬ ጋለሞታዎች ታጠቡበት።
ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።
በቀርሜሎስም ራስ ላይ ቢሸሸጉ እንኳ አድኜ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ እንኳ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፤