La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 66:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነፍሴን በሕይወት ያኖራታል፥ እግሮቼንም ለመናወጥ አልሰጠም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኛን በሕይወት የሚያኖረን፣ እግራችንንም ከመንሸራተት የሚጠብቅ እርሱ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱ በሕይወት ጠብቆናል፤ እንድንወድቅም አላደረገም።

Ver Capítulo



መዝሙር 66:9
13 Referencias Cruzadas  

ለዘለዓለም አይናወጥም፥ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል።


እግርህ እንዲናወጥ አይፈቅድም፥ የሚጠብቅህም አይተኛም።


ጻድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ የክፉዎች በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም።


መንግሥት ለጌታ ነውና፥ እርሱም አሕዛብን ይገዛል።


ሸክምህን በጌታ ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል፥ ለጻድቁም ለዘለዓለም ሁከትን አይሰጠውም።


ነፍሴ በጸጥታ እግዚአብሔርን ትጠብቅ የለምን? መድኃኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።


ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን በጸጥታ ጠብቂ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።


እግሮቼ ተሰናከሉ ባልሁ ጊዜ፥ አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ ረዳኝ።


ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ ‘እኛ ደግሞ ዘመዶቹ ነንና፤’ ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን፤ እንኖርማለን።


እርሱ የታማኞቹን እግር ይጠብቃል ሰው በኃይሉ አይበረታምና፥ ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይጣላሉ።


ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፥ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በጌታ ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፥ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል።